የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በጎንደር ከተማ የዓባይ ጋርመንት ፋብሪካን እየጎበኙ ነው።

83

ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው እና ሌሎች የክልሉና የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በጎንደር ከተማ የሚገኘውን ዓባይ ጋርመንት ፋብሪካ የሥራ እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው።

ዓባይ ጋርመንት ፋብሪካ የተለያዩ ጨርቃ ጨርቆችን የሚያመርት ትልቅ ፋብሪካ ነው። ፋብሪካው ለ700 ወገኖች የሥራ እድል ፈጥሯል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከክትባት ዘመቻው ጎን ለጎን የማህጸን በር ካንሰር ልየታም እየተሠራ መኾኑን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።
Next articleከ52 ሺህ በላይ ልጃገረዶች የማህጸን በር ካንሰር ክትባት እንደሚወስዱ የምዕራብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ገለጸ።