የፌደራል እና የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ጎንደር ከተማ ገቡ።

289

ጎንደርር: ኅዳር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ከፍተኛ መሪዎቹ ጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የሰሜን ምዕራብ እዝ አዛዥ ሌትናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና አባት አርበኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ በጎንደር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የጎንደርን ከተማ የውኃ ችግር ይፈታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የመገጭ ግድብ፣ የአዘዞ አርበኞች አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት፣ የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት እና ጥገና ሥራ፣ የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማትን የመሳሰሉ በከተማዋ እየተገገበሩ የሚገኙ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ይገኛሉ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለደሴ ከተማ የኮሪደር ልማት የይዞታ ቦታቸውን በደስታ መልቀቃቸውን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
Next articleበደሴ ከተማ የተማሪዎች ምገባ መርሐ ግብር ተማሪዎች ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ አስችሏል፡፡