ሕጻን ኪብሮን ደርበውን በማገት እና በመግደል የተጠረጠሩት ግለሠቦች ተፈረደባቸው።

67

ጎንደር: ኅዳር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሕጻን ኪብሮን ደርበውን በማገት እና በመግደል የተጠረጠሩት ግለሠቦች ከ21 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባስቻለው ችሎት ሕጻን ኬብሮንን በማገት እና በመሠወር አሠቃይተው ገድለዋል በተባሉት ጥፋተኞች ላይ ውሣኔ ሠጥቷል።

በዚህ መሠረትም፡-
1ኛ ተከሣሽ ወይዘሮ አበባ ዘለቀ አያሌውን በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ሲቀጣ
2ኛ አቶ ሙሉጌታ አታሎ ሲሳይ እና አቶ ያዛቸው ውብሥራ ኃይሌን በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ በወጭ ንግድ ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገበች መኾኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleጽዱ እና ውብ ከተማን መገንባት የሁሉም ማኅበረሰብ ክፍል ኀላፊነት ነው።