በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ዱርቤቴ ከተማ አሥተዳደር የተገነቡ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች እየተመረቁ ነው።

190

ባሕር ዳር: ኅዳር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሚመረቁት የመሠረተ ልማት ሥራዎች የከተማ አሥተዳደሩ ያስገነባቸውን ድልድይ፣ የመናኻሪያ መጸዳጃ ቤት፣ ለችግረኛ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶች፣ የመንገድ ዳር መብራት እና የውኃ ጽሕፈት የቢሮ ግንባታ ናቸው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሰፋ ጥላሁንን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ መሪዎች፣ የዱር ቤቴ ከተማ አሥተዳደር መሪዎች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደሴ ከተማ የኮሪደር ልማት የተግባር ሥራው ዛሬ በይፋ ተጀመረ።
Next articleበባሕር ዳር ከተማ የመንገድ መሠረተ ልማት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት አስታወቀ።