90 በመቶው የሰሊጥ ሰብል መሰብሰቡን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

35

ባሕር ዳር: ኅዳር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምርት ዘመኑ በአማራ ክልል ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ይጠበቃል።

በክልሉ በ2016/17 የመኽር ወቅት ከለማው ሰሊጥ 4 ሚሊየን 746 ሺህ 636 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በምርት ዘመኑ 458 ሺህ 264 ሄክታር መሬት በማልማት ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን በቢሮው የሰብል ልማት ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡

በተደረገው የተቀናጀ ርብርብም ከዕቅድ በላይ 593 ሺህ 329 ሄክታር ማልማት መቻሉን እና ከዚህም 4 ሚሊየን 746 ሺህ 636 ኩንታል የሰሊጥ ምርት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡

በአጠቃላይ በሰሊጥ ሰብል ከተሸፈነው ውስጥ እስከ አሁን 90 በመቶው መሰብሰቡን እና ቀሪው 10 በመቶ በመሰብሰብ ሂደት ላይ መኾኑን አረጋግጠዋል፡፡

ከዕቅድ በላይ ለመፈጸም ካስቻሉ ምክንያቶች መካከልም አንዱ በአኩሪ አተር ላይ የተፈጠረውን የገበያ ክፍተት ተከትሎ በርካታ አምራቾች ወደ ሰሊጥ ፊታቸውን ማዞራቸው መኾኑን ጠቅሰዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምዕራብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ለገለጎ ገንዳ ውኃ የአስፋልት መንገድ ግንባታ መሳለጥ እየሠራ ነው።
Next articleበደሴ ከተማ የኮሪደር ልማት የተግባር ሥራው ዛሬ በይፋ ተጀመረ።