በሰሜን ጎንደር ዞን ከ3 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ለመሠብሠብ እየተሠራ ነው፡፡

36

ደባርቅ: ኅዳር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ2016/17 የምርት ዘመን ከ3 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት ለመሠብሠብ ማቀዱን የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

መምሪያው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሠብል ላይ ጉዳት እያደረሰ መኾኑን ገልጾ አርሶ አደሩ የደረሱ ሠብሎችን በወቅቱ እንዲሠበሥብ አሳስቧል።

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በተለያዩ ቦታወች እየተከሰተ በመኾኑ ሠብላቸውን ከውድመት ለመጠበቅ በወቅቱ ሠብል እየሠበሠቡ መኾኑን የደባርቅ ዙሪያ ቀበሌ አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

አርሶ አደሮቹ በሠብል ሥብሠባ ወቅት እና በማጓጓዝ ሂደት የምርት ብክነት እንዳያጋጥም ከግብርና ባለሙያዎች ጋር ተቀራርበው እየሠሩ መኾኑንም አንስተዋል።

በመስክ ተገኝተው ድጋፍ ሲያደርጉ አሚኮ ያነጋገራቸው የግብርና ባለሙያ ነጋሽ አበራ አርሶ አደሩ ሠብሉን ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ እና ከምርት ብክነት ለመጠበቅ ከግብርና ባለሙያው ጋር ተቀራርቦ እየሠራ መኾኑን አንስተዋል።

በምርት ዘመኑ ከ153 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በዘር መሸፈኑን ያስታዎሱት የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ዮሐንስ ይግዛው ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሠብሠብ መታቀዱን ገልጸዋል።

አርሶ አደሩ በምርት ሥብሠባ ሂደት ብቻ ሳይኾን በሚያጓጉዝበት ወቅትም የምርት ብክነት ሊያጋጥም ስለሚችል ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ተመላክቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየማህጸን በር ካንሰር ክትባት በተሳካ መንገድ እንዲሰጥ ማኅበረሰቡ እንዲተባበር ጥሪ ቀረበ፡፡
Next articleከገንዳውኃ እስከ ቋራ እየተሠራ ያለው መንገድ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ነው።