
ባሕር ዳር: ኅዳር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶር) የሀገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ ምርታማነት ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ልማታችንን ከግብ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያችንን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት።
“ዛሬ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የሚመሩ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝቻለሁ። ዕሴት በተጨመረበት ቡና ኤክስፖርት እና ብረታ ብረት ምርት ላይ የተካነው ኤኤምጂ ሆልዲንግስ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በመስተዋት እና በአሉሚኒየም ሥራዎች የሚታወቀው አንድነት መስተዋት ቴክኖሎጂ የግሉ ዘርፍ ለኢንዱስትሪ መስፋፋት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽዖ ማሳያ ናቸው” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!