አስከፊውን የማሕጸን ጫፍ በር ካንሠር ለመከላከል ለልጃገረዶች ክትባት እየተሰጠ ነው።

51

ባሕርዳር: ኅዳር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የማህጸን ጫፍ በር ካንሰር የመከላከያ ክትባት “አስከፊውን የማሕጸን ጫፍ በር ካንሠር በሽታ በክትባት እንከላከል” በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ድልችቦ አጠቃላይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጀምሯል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የእናቶች ሕጻናት እና ወጣቶች ዳይሬክተር መልሰው ጫንያለው የማሕጸን ጫፍ በር ካንሰር ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በዓለም አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ካንሰሩ ከታወቀ በኋላ ድጋፍ እና እንክብካቤ ከማድረግ ባለፈ ሕክምና እንደሌለውም ነው የተገጸው። የማሕጸን በር ካንሰር ከሌሎች ካንሰሮች የሚለየው ቀድሞ በመለየት ክትባት መስጠት መቻሉ ነው።

ባለፉት ዓመታት ይገኝ የነበረው ክትባት መጠን ዝቅተኛ ስለነበር በስድስት ዓመታት መከተብ የተቻለው 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሴቶችን ብቻ መኾኑን ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት በቂ ክትባት በመገኘቱ ከ9 እስከ 14 ዓመት የሚገኙ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች በዚህ ዙር ይከተባሉ ነው የተባለው።

ክትባቱ እስከ ኅዳር 13/2017 ዓ.ም በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች በዘመቻ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሌማት ትሩፋት ከፍተኛ ለውጥ እያሳየ መኾኑን የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) ገለጹ።
Next article“ሰላምን የወደደ ሁሌም አሸናፊ ነው” አሸተ ደምለው