በአማራ ክልል ለሌማት ትሩፋት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑን ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) ገለጹ።

29

ደብረብርሃን: ኅዳር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የሚገኝ የዶሮ እርባታ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ሚኒስትሮች፣ የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት መሪዎች እና የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የተጎበኘው የደብረ ሆላንድ የደሮ እርባታ ማዕከል ነው።

በጉብኝቱ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) በክልሉ ለሌማት ትሩፋት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል። የሌማት ትሩፋት ለወጣቶች አንደኛው የሥራ ዕድል መፍጠሪያ መኾኑንም ገልጸዋል።

ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦ የከተማ አሥተዳደሮች ለሌላማት ትሩፋት የሚኾን ቦታ እያዘጋጁ ግንባታዎች እየተገነቡ መኾናቸውንም ተናግረዋል።

አንዳንዶቹ ደግሞ ግንባታቸው ተጠናቅቆ ወደ ሥራ መግባታቸውን ነው የገለጹት። ሥርዓተ ምግብን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል። ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሠማሩ ምቹ ኹኔታዎች መፈጠራቸውንም አመላክተዋል።

የደብረ ሆላንድ የደሮ እርባታ ማዕከል ዘርፉ ምን ያክል አዋጭ እና መንግሥትም ለዘርፉ ምን ያክል ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል። በክልሉ የጫጩት መፈልፈያ ለማስፋፋት እየተሠራ መኾኑንም አስታውቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአንድ ሄክታር መሬት ላይ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ገቢ የሚያስገኝ የኮረሪማ ቅመም እንደሚያመርቱ የጎፋ ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ።
Next articleየሌማት ትሩፋት ከፍተኛ ለውጥ እያሳየ መኾኑን የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) ገለጹ።