
ባሕር ዳር: ኅዳር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሚገኝ የዶሮ ርባታ ማዕከልን ጎበኝተዋል።
በጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የጦር ኀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ.ር)፣ የመንግሥት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር)፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴንን (ዶ.ር) ጨምሮ የክልሉ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። ዛሬ የተጎበኘው የደብረ ሆላንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ነው።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በከተማዋ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። “ከ650 በላይ ኢንዱስሪዎች በግንባታ እና በማምረት ሂደት ላይ ናቸው” ብለዋል።
የደሮ እርባታ ማዕከሉ ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጪ የተገነባ መኾኑን ገልፀዋል። በቀን እስከ 120 ሺህ እንቁላል ማምረት እንደሚችል የተናገሩት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አሁን ላይ በቀን 50 ሺህ እንቁላሎችን እያማረተ መኾኑን ገፀዋል። ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በእንስሳት ሃብት ትልቅ አቅም ያላት መኾኗንም ተናግረዋል።
የደሮ እርባታ ማዕከሉ ለአካባቢው እና ለማዕከላዊ ገበያ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው የተመላከተው።
የኢንዱስትሪ ፍሰቱ እየጨመረ ለመምጣቱ በከተማዋ እየተሰጠ ያለው ፈጣን አገልግሎት እና የማኅበረሰቡ ሰላም ወዳድነት መኾኑን ነው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የተናገሩት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!