
ባሕርዳር: ኅዳር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፈለገ ሕይዎት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በዐይን ሞራ ግርዶሽ እየተቸገሩ ያሉ የክልሉ ነዋሪዎችን በመለየት የቀዶ ጥገና ሥራ እየሠራ እንደኾነ ተገልጻል፡፡ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ በክልሉ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን አካባቢዎች ስለመለየቱም ነው የተብራራው፡፡
በጥናቱ መሠረትም ቻግኒ፣ እንጅባራ፣ ሞጣ፣ ሊበን፣ ዳንግላ፣ ከፎገራ ወረዳ ቁሀር ቀበሌ፣ ዱርቤቴ፣ ወረታ፣ ይስማላ እና ባሕር ዳር ችግሩ የተገኘባቸው አካባቢዎች ስለመኾናቸው ነው የተገለጸው።
የተለዩ ሕሙማንም ለቀዶ ጥገና እንዲዘጋጁ መደረጉ ነው የተብራራው፡፡ የፈለገ ሕይዎት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከኪዮር ብላይንድነስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የቀዶ ጥገናው እንደሚሠራም ታውቋል፡፡ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ እስካኹን ከ12ሺህ በላይ ታካሚዎች ቀዶ ጥገና ስለመደረጉም ነው የተገለጸ።
እየተካሄደ ያለው የዐይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ጥገና ሕክምና እስከ ኅዳር 12/2017 ዓ.ም እንደሚቆይም ታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!