
የተትረፈረፈ የምግብ ምርት ለማምረትና የተመጣጠነ የምግብ ዋስትና ስርዓትን ለማረጋገጥ በሁሉም መስክ የተጀመሩ ሥራዎች የሚበረታቱ ናቸው።
በደብረ ብርሃን ከተማ የጎበኘነው የደብረ ሆላንድ የዶሮና እንቁላል ምርት ማዕከልም ሀገራዊ ውጥናችንን ለማሳካት የሚያግዝ ነው።
ማዕከሉ ከ90 ሺህ በላይ እንቁላል በየቀኑ እያመረተ መሆኑ ደግሞ ለገበያ በቂ ምርት እንዲቀርብ እና በአነስተኛ ዋጋ ለተጠቃሚ እንዲደርስ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
የውጭ ባለሀብቶች በሌማት ትሩፋት ሥራ ተሰማርተው ማየታችን ኢኒሼቲቩ ለኢንቨስትመንት ምቹ እንደሆነም የሚያረጋግጥ ነው።