የገንዳ-ውኃ ወጣት ማኅበራት ከኅብረተሰቡ በሰበሰቡት 86 ሺህ ብር በዓልን ለማክበር ለተቸገሩ ነዋሪዎች ድጋፍ አደረጉ።

98

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 11/2012 ዓ.ም (አብመድ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ-ውኃ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ወጣት ማኅበራት በዓሉን ለማክበር የአቅም ችግር ለነበረባቸው 450 ሰዎች የበዓል መዋያ ሥጋ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ወጣቶቹ ከኅብረተሰቡ ሰበሰቡት 86 ሺህ ብር ውስጥ በ60 ሺህ ብር ወጭ አራት ላሞችን ገዝተው በማረድ ስጋ አከፋፍለዋል። ቀሪው ገንዘብ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ለሚጎዱ ሰዎች ድጋፍ እንደሚደረግበት ገልጸዋል።

ገንዘቡ የተሰበሰበው ከከተማው ነዋሪዎች መሆኑን የገንዳ-ውኃ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ሊቀ መንበር ደጀን ቢራራ አስታውቋል፡፡ ከጥሬ ገንዘቡ በተጨማሪም ሁለት ተቋማት ሦስት ፍዬሎችን እንደሰጡ ገልጿል። ከከተማዋ ነዋሪዎች በተጨማሪም በኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የ33 ክፍለ ጦር አንደኛ ብርጌድ 2 ሺህ 225 ብር እና 230 ኪሎ ግራም ፊኖ ዱቄት እንደደገፏቸው ሊቀ መንበሩ አስታውሶ ምሥጋና አቅርቧል።

ዘጋቢ፡- ዳንኤል ወርቄ -ከገንዳ-ውኃ

Previous articleየኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በተለየ መልኩ በየቤቱ እየተከበረ ነው፡፡
Next articleየኮሮና ወረርሽኝ ብዙ ሠራተኞችን እስከወዲያኛው ከሥራ እንዳያሰናብት ተሰግቷል፡፡