የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ መርሐ ግብር በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በእንጅባራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

140

እንጅባራ፡ ኅዳር 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ መልዕክት እየተካሄደ በሚገኘው በዚኹ መርሐ ግብር ከእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር፣ ከባንጃ ወረዳና ከብሔረሰብ አሥተዳደሩ የተወከሉ የፓርቲው አባላት፣ ደጋፊዎች እና መሪዎች ተገኝተዋል።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አለሙ ሰውነት “ብልጽግና ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ ሥኬቶችን ያስመዘገበ፣ ያጋጠሙ ፈተናዎችን ኹሉ ወደ ድል እየቀየረ የመጣ ፓርቲ ነው” ብለዋል።

ፓርቲው የቆዩ የሁከት እና የብጥብጥ የፖለቲካ ልምምዶች በሃሳብ ልዕልና እንዲዳኙ ለማድረግ የጀመራቸው ሥራዎች ውጤት የታየባቸው እንደኾነም ኀላፊው አንስተዋል።

በዓሉ በሁሉም ወረዳዎች እና ከተሞች በሕዝባዊ ውይይቶች፣ ሥልጠናዎች እና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷልም ነው ያሉት። የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴወድሮስ እንዳለው ብልጽግና በሃሳብ ልዕልና የሚያምን ግንባር እና አጋር የሚል የሞግዚት ፌዴራሊዝም ሥርዓትን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅሎ የጣለ አካታች ፓርቲ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በሀገራቸው ጉዳይ እኩል የመወሰን እና የመልማት መብትም ፓርቲው ካጎናጸፋቸው ዕድሎች መካከል እንደኾነም ዋና አሥተዳዳሪው አንስተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የጤናውን ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ለማሳደግ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን አቅም ማጎልበት ይገባል” የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
Next articleየደብረ ማርቆስ (መንቆረር) ከተማ መሥራች ደጃዝማች ተድላ ጓሉ!