“የጤናውን ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ለማሳደግ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን አቅም ማጎልበት ይገባል” የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

60

ደብረ ብርሃን፡ ኅዳር 07/2017 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ማኅበረሰቡን ያሳተፈ ውይይት እያደረገ ነው።

የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ቴዎድሮስ ክፍለ ዮሐንስ (ዶ.ር) የመርሐ ግብሩ ዓላማ ጥራቱን የጠበቀ ሕክምና ለመስጠት ከኅብረተሰቡ እና ከአጋር አካላት ጋር ግብዓት ለማሰባሰብ ታስቦ መኾኑን ገልጸዋል።

በጤና ሳይንስ ካምፓሱ የሐኪም ግዛው ሆስፒታል የተሻለ የላበራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት በሠራው ሥራ ዕውቅና ያገኘ ላበራቶሪ መኾኑን አንስተዋል። በቀጣይም የተርሼሪ ኬር ሆስፒታል ለመገንባት የቦታ ልየታ እየተከናወነ መኾኑን ተናግረዋል።

የሆስፒታሉን የአገልግሎት አሰጣጥ አሰመልክቶ የማኅበረሰብ ተወካዮች ሃሳባቸውን ጠይቋል። ሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጡን እያዘመነ በመምጣቱ አማራጭ የጤና ተቋም እንደኾነላቸውም ሃሳባቸውን ነግረውናል።

የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ያለተቋም መኾኑን አንስተዋል። “የጤና ዘርፍን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሳደግ የመመርመሪያ መሣሪያዎችን አቅም ማጎልበት ይገባል” ብለዋል።

የጤና አገልግሎቱ የተሻለ እንዲኾን የላበራቶሪ አገልግሎቱ ላይ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ ወርቃለማው ኮስትሬ የሃኪም ግዛው ሆስፒታል ለከተማዋ ነዋሪዎች የላቀ አገልግሎት በመስጠት ላይ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ ፋንታነሽ መሐመድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አምራቹን በቀጥታ ከሸማቹ ለማገናኘት ጊዜያዊ እና ቋሚ የገበያ ማዕከላትን የማስፋፋት ሥራ እየተሠራ ነው” ኢብራሂም መሐመድ (ዶ.ር)
Next articleየብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ መርሐ ግብር በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በእንጅባራ ከተማ እየተካሄደ ነው።