
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌድሪ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫውን የሰጡት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) “ቱሪዝም ለዘላቂ ሀገራዊ እድገት ዋና የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እየተሠራበት ነው” ብለዋል።
ለዚህም አስፈላጊዉ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፤ አጠናክረንም እንቀጥልበታለን ነዉ ያሉት። በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እየተሠሩ ያሉት የገበታ ለሀገር ልማቶች ለዚህ ማሳያዎች ናቸዉ ብለዋል። እነዚህ ተግባራት ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም በመግለጫዉ ተመላክቷል፡፡
ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችንም ሀገራችን እየሳበች ስለመኾኑ ተመላክቷል። ለዚህ ደግሞ ባሳለፍነዉ ጥቅምት ወር የተካሄዱ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች ማሳያዎች ናቸዉ ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ይህ ደግሞ ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድረገን ከሠራን ዉጤታማ የሚያደርገን መኾኑን አመላካች ነው ብለዋል። በቀጣይም የቱሪዝም ዘርፉ የሥራ እድል በሚፈጥር እና ኢኮኖሚዉን በሚያሳድግ መልኩ በትኩረት ይሠራበታል ተብሏል በመግለጫዉ፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!