
አዲስ አበባ: ኅዳር 07/2017 ዓ.ም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሀገሪቱን አሁናዊ ሁኔታ እና የቀጣይ አቅጣጫን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው “በከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ፤ የከተሞችን የቱሪዝም አቅም ለማሳደግ የሚያግዙ መኾናቸውን” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራዎቹ ዜጎችን በሚያፈናቅል መልኩ የሚሠሩ ተደርጎ የሚነሳው ሃሰተኛ መረጃም የሀገሩቱን ልማት እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ለውጥ በማይፈልጉ ኀይሎች የሚፈጸም ነው ብለዋል።
ዶክተር ለገሰ የልማት ሥራዎቹን መንግሥት በከተሞች የሚኖሩ ዜጎችን ሕይዎት ለማሻሻል ባለመ መልኩ የሚፈጽማቸው መኾኑን ጠቅሰው በቂ ዝግጅት የተደረገባቸው መኾኑንም ጠቁመዋል።
በኮሪደር ልማቱ የወንዝ ዳር ልማት፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ መንገድ፣ የመኖሪያ ስፋራዎች እና ከተሞቸን የሚመጥኑ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ግዑሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!