
አዲስ አበባ: ኅዳር 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌድሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫዉን የሰጡት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) መንግሥት በዘር የተሸፈነው መሬት በተገቢው ሰዓት እንዲሠበሠብ እየሠራ ነው ብለዋል። እስካሁንም 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ሰብል በአግባቡ ተሠብሥቧል ብለዋል።
አሁንም በሰብል አሠባሠብ ሂደቱ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የበኩሉን እንዲወጣ ያሳሰቡ ሚኒስትሩ በዚህ በጀት ዓመትም መንግሥት የግብርና ዘርፉን ለማዘመን እየሠራ ነው ብለዋል።
የምርት ብክነት እንዳይኖር ማድረግ፣ የሌማት ቱሩፋት፣ የበጋ መስኖ ስንዴ፣ መካናይዜሽን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሠራባቸው ዘርፎች መኾናቸውን ጠቅሰዋል።
የኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በ2017 ዓ.ም የምርት ዘመን የአርሶ አደሩን መሬት በዘር ለመሸፈን በቂ ዝግጅት መደረጉን አንስተው የግብርና ግብዓት አቅርቦት ሥራም በበቂ ተሰርቷል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ግዑሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!