ኢትዮጵያ ከታንዛንያ ጋር ዛሬ ትጫወታለች።

58

ባሕር ዳር: ኅዳር 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በ2025 ሞሮኮ ላይ ለሚደረገው የአፍሪካ ወንዶች እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ ስምንት የተደለደሉት ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ዛሬ ይጫወታሉ።

ጨዋታው በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ርእሰ መዲና ኪንሻሳ በሚገኘው ስታድ ደ. ማርትየርስ ስታዲየም ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከላይ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ መለያ ለብሶ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ለማወቅ ተችሏል።

የታንዛንያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ቢጫ በሰማያዊ መለያ ይጠቀማል ነው የተባለው።

ኢትዮጵያ እስካሁን አራት የማጣሪያ ጨዋታዎችን አድርጋ ከታንዛንያ ጋር ያለምንም ግብ አቻ በመለያየት አንድ ነጥብ ብቻ ይዛ ትገኛለች።

ምድቡን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በ12 ነጥብ ትመራዋለች። ጊኒ በስድስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ታንዛንያ በአራት ነጥብ ሦስተኛ ላይ ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ በአንድ ነጥብ ከምድቡ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ዋልያዎቹ ኀዳር 10/2017 ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋርም ይጫወታል ሲል ካፍ ኦን ላይን በድረ ገጹ አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ወንጀለኞችን በሕግ እንዲጠየቁ ማድረጉን አስታወቀ።
Next articleበጻግቭጂ ወረዳ ለሚገኙ የተቸገሩ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ተደረገ።