
ባሕር ዳር: ኅዳር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ ከ156 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጪ ለደብረ ታቦር ከተማ አግልግሎት የሚኾን የንፁህ መጠጥ ውኃ ጉድጓድ አጠናቅቆ አስረክቧል። 11 ኪሎ ሜትር የውኃ መስመር ዝርጋታም ተጠናቅቆ ዛሬ ተመርቋል።
የንፁህ መጠጥ ውኃ ጉድጓድ እና የመስመር ዝርጋታው ተጠናቅቆ “ታሪካዊ ስጦታ ለታሪካዊቷ ከተማችን” በሚል መሪ መልዕክት የመጀመሪያ ዙር ርክክብ አድርጓል።
በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የደብረ ታቦር ከተማ፣ የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የዮኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!