የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ሀገራዊ ትብብርን በሚያሳድግ መልኩ ለማክበር መዘጋጀቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስታወቀ።

41

አዲስ አበባ: ኅዳር 6/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሕገ-መንግሥቱ የተገኙ መብቶችን ለማጠናከር የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ገልጿል። 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓልን አስመልከቶ መግለጫ ተሰጥቷል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፀሐይ ወራሳ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል በሕገ-መንግሥቱ እንዲከበር ከተወሰነበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ዓመታት የሕዝብን አንድነት እና እርስ በእርስ የማስተሳሰር ሥራ ሢሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።

አፈ-ጉባኤዋ በዓሉ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የራሱ ሚና ያለው በመኾኑ አንደ ክልል ያሉትን የኢንቨስትመንት እና የሰላም ፀጋዎች ለማስተዋወቅ ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ይህም ኅብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝምን ማጎልበት የሚያስችል አቅም ይፈጥራል ነው ያሉት።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አዳማ ትንጳዪ በዓሉ ከዚህ በፊት የነበሩ የተዛነፉ አካሄዶችን ለማረም ዕድል የሚገኝበት እንደኾነም አስረድተዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሀገር ደረጃም በርካታ ብሔረሰቦች የሚኖሩበት ክልል በመኾኑ ለብዝኅነት ተግባራዊ ማሳያ መኾኑን አንስተዋል፡፡ በሕገ-መንግሥቱ የተገኙ መብቶችን ለማጠናከርም በዓሉ ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል።

ሕዝቦች ለዘመናት የታገሉበት ፍሬ አፍርቶ ዜጎች ማንነታቸው፣ ቋንቋ እና ባሕላቸው አንዲከበር ያስቻለ በዓል በመኾኑ ሊታወስ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን- ከአርባምንጭ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምሁራን ለሀገራዊ ችግሮች የጋራ መፍትሄ ማምጣት ላይ የመሥራት ሙያዊ እና ታሪካዊ ኀላፊነት አለባቸው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
Next articleዓለም አቀፍ የጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች ኮንፈረንስ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።