“ምሁራን ለሀገራዊ ችግሮች የጋራ መፍትሄ ማምጣት ላይ የመሥራት ሙያዊ እና ታሪካዊ ኀላፊነት አለባቸው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

36

አድስ አበባ: ኅዳር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 51 የመንግሥት እና አምስት የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሚሳተፉበት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘመናት በተለያዩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ችግሮች ውስጥ በጽናት ያለፈች ሀገር ናት ያሉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ላለመግባባት ምንጭ የኾኑ እንደ ግጭት እና ጦርነት ያሉ ሰው ሠራሽ ችግሮች መንስኤ እኛው እንደመኾናቸን የመፍትሄ አካልም እኛው ኾነን መገኘት አለብን ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት “ምሁራን ለሀገራዊ ችግሮች የጋራ መፍትሄ ማምጣት ላይ የመሥራት ሙያዊ እና ታሪካዊ ኀላፊነት አለባቸው” ብለዋል። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማኅበረሰብ ክፍሎች አንድ አካል እንደ መኾናቸው በምክክር ሒደቱም የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ዋና ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

በመድረኩ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው በቀጣይ ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር በጋራ መሥራት በሚያስችለው ጉዳይ ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። በምክክሩ ከ1 ሺህ 200 በላይ ምሁራን ተሳታፊ መኾናቸውም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጤናው ዘርፍ መሠረተ ልማት ሥራዎችን በማሟላት ሞትን ለመቀነስ በትኩረት እየተሠራ ነው።
Next articleየብሔር ብሔረሰቦች በዓል ሀገራዊ ትብብርን በሚያሳድግ መልኩ ለማክበር መዘጋጀቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስታወቀ።