ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሥራ ጉብኝት ባሕር ዳር ከተማ ገቡ።

147

ባሕር ዳር: ኅዳር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሥራ ጉብኝት ባሕር ዳር ገብተዋል።

ፊልድ ማርሻሉ ባሕር ዳር ሲገቡ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ ሌሎችም የክልሉ እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች እና ነዋሪዎችም ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በባሕር ዳር ቆይታቸው በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይም የክልሉን ሕዝብ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ውይይቶችን ያደርጋሉ። ከዚህ በተጨማሪም በባሕር ዳር ከተማ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው እንደሚመለከቱ ይጠበቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች ዕውቅና እና ሽልማት አበረከተ፡፡
Next articleየጤናው ዘርፍ መሠረተ ልማት ሥራዎችን በማሟላት ሞትን ለመቀነስ በትኩረት እየተሠራ ነው።