የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በሥነ ምግባሩ ብቁ፣ ታማኝ እና ሀገሩን የሚወድ ትውልድ ማፍራት እንደሚገባ ሙሉነሽ ደሴ ( ዶ.ር) አሳሰቡ።

63

ባሕር ዳር: ኅዳር 5/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን “የትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታን ለማጠናከር ከትምህርት ዘርፉ መሪዎች፣ ከትምህርት ቤት ርእሳነ መምህራን አና ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር ያዘጋጀውን የምክክር መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እንደ ሀገር እና ክልል የገጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በሥነ ምግባሩ ብቁ፣ ታማኝ እና ሀገሩን የሚወድ ትውልድ ማፍራት ይገባል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ ትምህርት ቤቶች ዋነኛውን ሚና መጫዎት አለባቸው ነው ያሉት።

በሥነ ምግባር ያልታገዘ ትምህርት ጥፋት ያመጣል ነው ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ፡፡ ትምህርት ቤቶች ትውልዱ ለትንንሽ እንቅፋቶች የማይገፋ፣ ነገ ላይ ትኩረት ያደረገ እና ሀገር ወዳድ እንዲኾን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተናበው ከሠሩ አዎንታዊ ለውጥ ይመጣል ብለዋል።

የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሐብታሙ ሞገስ የሚስተዋለውን የሥነ ምግባር ችግር ለማስወገድ በየትምህርት ቤቶች በባለሙያ የተደገፈ የሥነ ምግባር ትምህርት እንደሚሠጡም ገልጸዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል ለማድረግ ወሳኝ ነው።
Next articleየብሔር ብሔረሰቦች በዓል ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ መኾኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስታወቀ።