
ባሕር ዳር: ኅዳር 5/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የገጠር ዘርፍ ጉድኝት ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን እየገመገሙ ነው።
በግምገማ መድረኩ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አቤዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) እና የየተቋማቱ ከፍተኛ መሪዎች እንዲሁም የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።
የተቋማቱ ያለፈው ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በሚገመገምበት በዚሁ መድረክ ከመደበኛ ሥራ በተጨማሪ ለሰላሙ ያላቸውን አበርክቶ የሚዳሰስ ሲኾን በቀጣይ ጊዜ ተግባራት ላይም አቅጣጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!