በሰሜን ጎንደር ዞን ከ6 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ወጣቶች የመሠረታዊ ዲጅታል ክህሎት ሥልጠና ለመስጠት እየተሠራ ነው፡፡

53

ደባርቅ: ኅዳር 4/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለወጣቶች የዲጅታል ዕውቀትን ማዳበር ለሀገራዊ አካታች ዕድገት ወሳኝ መኾኑን የሰሜን ጎንደር ዞን ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ አስታውቋል።

የዞኑ ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ ለመሪዎች የኢትዮ ኮደርስ መርሐ ግብር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የዕቅድ ትውውቅ አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዲያቆን ሸጋው ውቤ የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና “ወጣቶች በዲጅታል ማንበብ እና መፍጠር እንዲችሉ በማድረግ ለሀገራዊ የዲጅታል ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እና ተጠቃሚ እንዲኾኑ ያስችላቸዋል” ብለዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ደገፋው ታከለ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ እና የዲጅታላይዜሽን ልማት ለሀገር ዕድገት ዓይነተኛ መሳሪያ በመኾኑ የዲጅታል ክህሎት ያለው ማኅበረሰብ መፍጠር ለነገ የማይባል ተግባር እንደኾነም አስረድተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከ6 ሺህ 600 በላይ ለሚኾኑ ወጣቶች የመሠረታዊ ዲጅታል ክህሎት ሥልጠና ለመስጠት መታቀዱንም ገልጸዋል።

ሥልጠናው በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣ በመንግሥት እና የግል ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች ተመሳሳይ ማዕከላት እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት መገምገማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ።
Next articleታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት ምሕረት ጠይቀው መግባታቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር አስታወቀ።