
ባሕር ዳር: ኅዳር 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስተሩ በተገኙበት ተገምግሟል።
ዛሬ በስምንት የኮሪደር አቅጣጫዎች እና 2 ሺህ 879 ሄክታር በሚሸፍን ስፋት ላይ እየተሠራ ያለውን የሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት ገምግመናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት።
ከተማዎቻችንን ለእድገት እና ለኑሮ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ ለመራመድ ተችሏል።
አሁን በሶስት መሠረታዊ ኃላፊነቶች ላይ ማተኮር ይገባናል። በመጀመሪያ ለቀጣዩ ትውልድ ፍላጎት የተስማሙ ከተሞችን መገንባት፤ ሁለተኛ በመለወጥ ላይ ባሉት ከተሞች ከፍ ብሎ ማደግ የሚችል ትውልድ መቅረጽ፤ ሶስተኛም እነዚህን የዘመኑ ከተሞች በልህቀት ለመምራት የተዘጋጀ አመራር ኮትኩቶ ማብቃት ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!