ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እያከናወነቻቸው ላሉ ሥራዎች ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ አሳሰቡ።

23

ባሕር ዳር : ኅዳር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለመከላከል እየተገበረቻቸው ላሉ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገልጸዋል።

በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ በሚገኘው 29ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ(ኮፕ 29) ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን ጨምሮ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና እንክብካቤ የምታደርጋቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስረድተዋል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲህ አይነት መሰል ጥረቶች እንዲጎለብቱ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበየደረጃው የተፈጠረው የውይይት መድረክ ለግብር አሠባሠቡ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የደቡብ ጎንደር ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ፡፡
Next articleየኮሪደር ልማቱ ለብዙዎች የሥራ እድል አስገኝቷል።