
ባሕር ዳር : ኅዳር 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) #COP29 እየተካሄደ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ጉዳይን መፍትሔ ለማስገኘት የሚከናወኑ ተግባራት ፋይናንስን ኢላማ ከማድረግ ባሻገር ሠርታለች ብለዋል። ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያራምዱ የጋራ ግን በነፍስ ወከፍ የተለዩ ኃላፊነቶችን ብሎም ታሪካዊ ተጠያቂነትን የሚያጠይቁ መኾን እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥታለች ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ግልፅነት ያላቸው የአየር ንብረት የገንዘብ ድጋፍ ብያኔዎች እድገትን እንደ አፍሪካ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዝቅተኛ የልማት መጠን ያላቸው ሀገራትን በተጨባጭ ለመከታተል አስፈላጊ ናቸው። ኢትዮጵያ የፓሪስ ስምምነትን እና የባለፈውን ዓመት የCOP28 ኃላፊነቶቿን በሦስት ሥራዎች እየተገበረች ትገኛለች ብለዋል።
ቀዳሚው የአረንጓዴ አሻራ ሥራ 40 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋን ከነበረበት በ6 በመቶ እንዲያድግ አድርጓል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት። ሌላው በ2015 የምርት እጥረትን ወደ ትርፍ ምርት የለወጠው በመስኖ የለማ ስንዴ መርሐ ግብር መኾኑንም አስታውቀዋል።
በታዳሽ የኃይል ምንጭ የታገዙ የእግረኛ መንገዶች ያሏቸው እና የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች የቀረቡባቸው ዘላቂና አረንጓዴ ከተሞችን የፈጠሩ ለአየርንብረት ጥበቃ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ የከተማ ልማት ፕሮጀክቶች ሌላዎቹ ሥራዎች መኾናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!