
አዲስ አበባ: ኅዳር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት የ19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በአል መሪ ሀሳብ ትንተና ውይይት እያካሔደ ነው።
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የእኔ ብቻ ባሕል ማንነት የሚል ነጠላ ትርክት ሀገራዊ አንድነት የማያመጣ በመኾኑ የእኔ ብቻ ከሚል አስተሳሰብ መውጣት ያስፈልጋል ብለዋል።
የብሔር ብሔረሰብ ቀን በዓል አንድነትን እና ኅብረ ብሔራዊነትን በማጎልበት ሁሉም ለሥራ እንዲነሱ ማድረግ ነው ብለዋል።
አፈ ጉባኤው በዚህ በኩል ላለፉት 18 ዓመታት የተከበረው በዓል ተገቢ ግንዛቤዎችን የፈጠረ ነበር ብለዋል።
“ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው 19ኛው በዓል የሚከበረው። መሪ ሀሳቡ ሲመረጥ ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን ሁኔታ የሚያመላክት እና ቀጣይ ሊኖራት የሚገባውን ኅብረት የሚያመላክት መኾኑን ጠቅሰዋል።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!