በደብረሲና ከተማ የእየተሠሩ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የሥራ እድል በመፍጠር ውጤታማ መኾናቸው ተገለጸ።

54

ደብረ ብርሃን: ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረሲና ከተማ አሥተዳድር የተሠሩና በመሠራት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ የክልል አመራሮች፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ፣ የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደሩ አመራሮች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፍቅረማርያም ደጀኔ በጉብኝቱ ወቅት በደብረሲና ከተማ አሥተዳድር የተሠሩና እየተሠሩ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች “ይቻላል ብለን ከተነሳን የማንሻገረዉ ችግር” እንደሌለ ማሳያ ናቸዉ ብለዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ ብርቃብርቅ ተሾመ በዞኑ ካሉ ከተማ አሥተዳድሮች በችግር ዉስጥም ኾኖ ጥሩ አፈፃፀም ካሳዩ ከተማ አሥተዳደሮች አንዱ ደብረሲና ከተማ አሥተዳድር መኾኑን ገልፀዉ የተሠሩና እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ይበል የሚያሰኙ ናቸዉ ብለዋል።

የደብረሲና ከተማ አሥተዳድር ከንቲባ ወንድምሲገኝ ማሙዬ የተሠሩና እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ለከተማዋ ዕድገት ወሳኝ መኾናቸዉን ገልፀዋል። በሥራ እድል ፈጠራዉም ዓይነተኛ ሚና ተጫዉተዋል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ ተሠርተው ከተጠናቀቁት መካከል የውኃ ማፋሰሻ ቦዮች ፣ ሁለት ትልልቅ ድልድዮች፣ በሰሜኑ ጦርነት ቤታቸዉ ፈርሶባቸዉ ለነበሩ ግለሰቦችና ዝቅተኛ ነዋሪዎች የተገነቡ ቤቶች እና የብሎኬት ፋብሪካ የጉብኝቱ አካል ነበሩ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከታሪክ ተወቃሽነት ለመውጣት ተረባርቦ ክልሉን ከችግር ማዳን ይጠበቃል” ምክትል ኮሚሽነር እንየው ዘውዴ
Next articleየጤና ተቋማት ጥራቱን የጠበቀ የላብራቶሪ አገልግሎት እንዲሠጡ ማስቻል የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ መኾኑን አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ አስገነዘቡ፡፡