በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።

83

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ከ61 ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር በላይ በኾነ ወጭ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።

የኩታበር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃ፣ የዲጂታል ላይብረሪ እንዲሁም የኩታበር ጤና ጣቢያ የእናቶች የወሊድ ኦፕሬሽን አገልግሎት የሚሰጥ የሕክምና ቁሳቁስ የተሟላለት ብሎክ ከተመረቁት መካከል ይገኙበታል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር )፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር )፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አማካሪ ባዘዘው ጫኔ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን እና ሌሎች የክልል እና የዞን መሪዎች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleግጭትን መጥላት እና ለሰላም ተግባራዊ ምላሽ መሥጠት እንደሚገባ ተገለፀ።
Next articleየመንግሥት ተቋማት የከተማ ግብርና ተሞክሮ ማሳያ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ።