በመሬት ወረራ የተሳተፉ ግለሰቦችን ለሕግ እያቀረበ መኾኑን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።

110

ባ/ዳር: ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተገን በማድረግ በባሕር ዳር ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ የመሬት ወረራ መታየቱን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው ተናግረዋል። ሕገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴም በስፍት መሰተዋሉን አንስተዋል።

እንደ ክልል የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተገን ተደርጎ በባሕር ዳር ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ የመሬት ወረራ እየተካሄደ ነበር ያሉት ኮማንደር ዋለልኝ በከተማ ደረጃ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ተጣርቶ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

ከኅብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረትም በመሬት ወረራ የተሳተፉ 17 ግለሰቦች እና ሁለት መሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራው ተጣርቶ ለፍርድ ቤት መቅረባቸውን ኮማንደር ዋለልኝ ተናግረዋል።

ኮማንደሩ አያይዘውም ያለአግባብ የተከዘኑ ሸቀጣሸቀጦች እንዲወረሱ ተደርጓል ነው ያሉት።

“በከተማዋ እስከ ገጠር ቀበሌዎች ድረስ ያሉ መንገዶች ክፍት በመኾናቸው ማንኛውም ሰላማዊ ማኀበረሰብ እንደ ፈለገ ተንቀሳቅሶ መሥራት ይችላል” ብለዋል።

በከተማዋ በተደረጉ 91 የውይይት መድረኮች ኀብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን በመቆም ሕገ ወጥ ተግባርን እና ሕገ ወጦችን በማጋለጥ እንደሚተባበር ሰፊ ይኹንታ ማሳየቱን ኮማንደሩ አስታውሰዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰላም ሁሉም በጋራ ቆሞ የሚጠብቃት የጋራ ሃብት ናት” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleለሰላም አንደኛው ሟች ሌላኛው ተመልካች መኾን እንደማይገባው ተገለጸ፡፡