
ጎንደር: ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ ተገኝተው ከነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው።
በውይይቱ ላይ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኛውን ጨምሮ ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች እየተሳተፉ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!