
ባሕር ዳር: ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው እንዳስታወቁት ዛሬ የመንግሥት አግልግሎትና አሥተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡
በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችን መጎብኘታቸውን ጠቁመዋል። የመጀመሪያው ዙር የቀዳሚ ምዕራፍ ሥራዎቻችንን በዚህ ምዕራፍ የተካተቱ ስምንት ተቋማት በተገኙበት ገምግመናል ነው ያሉት፡፡
በቀጣይም መልካም ጅምሮቻችንን አጠናክረን ማስቀጠል እና በሪፎርሙ የታቀፉ ተቋማትም ያላቸውን ልምዶች የሚቀያየሩበት አውድ መፍጠርም ተችሏል ብለዋል፡፡
ተቋማት ያከናወኗቸውን ተግባራት በዝርዝር በመቃኘት ጥንካሬዎችን፣ ውስንነቶችና በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ላይም አቅጣጫ አስቀምጠናል ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!