ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥትን የእድሳት ሥራ እየተመለከቱ ነው።

76

ጎንደር: ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ እየተዘዋወሩ የተለያዩ ልማቶችን የሥራ እንቅስቃሴ በመመልከት ላይ ናቸው ።

ዛሬ ጠዋት የመገጭ መሥኖ ፕሮጀክትን በተቋራጭነት ከሚሠራው ቢአይካ ባለቤት አቶ ካሳሁን ምስጋናው ጋር በኾን የፕሮጀክቱን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተው የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ በከሰዓት መርሐ ግብራቸው ደግሞ የአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥት የእድሳት ሥራን እየተመለከቱ ነው። የምልከታቸው ዓላማም የቱሪስቶች ሁነኛ መስብ የኾነው ይህ ቅርስ ደረጃውን ጠብቆ እና በፍጥነት እንዲታደስ ለማስቻል ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭን መስኖ ግድብ ፕሮጄክት እየተመለከቱ ነው።
Next articleከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ በሚኾን ወጭ የተገነባ ሸድ ለተጠቃሚ መተላለፉን የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ገለጸ፡፡