
ጎንደር: ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭን መስኖ ግድብ ፕሮጄክት የግንባታ እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው። ርእሰ መሥተዳድሩ የፕሮጀክቱን ተቋራጭ ባለሃብቶችን ጨምረው በጎንንደር ከተማ በመገኘት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ምልከታ ነው እያደረጉ የሚገኙት።
ርእሰ መሥተዳድሩ በቆይታቸው በከተማዋ እና በአካባቢው እየተከናወኑ የሚገኙ ትልልቅ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው እንደሚመለከቱ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
