
ባሕር ዳር: ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በ2017/18 የምርት ዘመን ከውጭ ከሚገዛው 23 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 472 ሺህ 500 ኩንታል ዩሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ ኤም ቪ ዓባይ ሁለት የተሰኘች የኢትዮጵያ መርከብ ጅቡቲ ወደብ ደርሳለች።
በቀጣይ ቀናትም የሰው ሠራሽ ማዳበሪያውን ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራም በፍጥነት እንደሚጀመር ይጠበቃል።
ለ2017/18 የምርት ዘመን ለ23 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪ ግዥ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመድቧል።
እንደ ኢፕድ ዘገባ መንግሥት አዲስ የግዥ መመሪያ በማውጣቱ ባለፈው የምርት ዘመን 21 ቢሊዮን ብር ለማዳን መቻሉን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!