“ዓለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ ኹኔታወችን ለመረዳት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች ወሣኝ ናቸው” የመንግሥት ሠራተኞች

64

ደባርቅ : ጥቅምት 28/2017 ዓ/ም (አሚኮ) በዞኑ “የኽልም ጉልበት ለእመርታዊ ለውጥ” በሚል መሪ መልዕክት በመምሪያው ለሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ሥልጠና ተሰጥቷል።

የሥልጠናው ተሳታፊዎች እንደገለጹት “ዓለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ ኹኔታወችን ለመረዳት ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች ወሣኝነት አላቸው ብለዋል።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተሠጣቸው ሥልጠናም ሀገራችን ላይ ያለውን ነባራዊ ኹኔታ እንድንረዳ የሚያግዝ ነው ሲሉም ገልጸዋል ።

የሰሜን ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መሠረታዊ የመንግሥት ሠራተኛ ፓርቲ አባላት ሠብሣቢ ሊጋባው ዘመነ “ሀገር የምትቀየረው በሥራ ነው፤ ለመሥራት ደግሞ መማር እና መሠረታዊ የግንዛቤ አድማስን ማስፋት ወሳኝ” ብለዋል።

ሠልጣኞቹ በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን ሥልጠና በአግባቡ ወደ ተግባር መቀየር እና ማኅበረሰቡን ማገልገል እንዳለባቸውም አሳስበዋል ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምርት ማምረት ዕድገት ብቻ ሳይኾን ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳይ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleአርሶ አደሮች በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በሚያከማቹት የምርት ደረሰኝ ብድር እየተመቻቸላቸው መኾኑ ተገለጸ።