“ምርት ማምረት ዕድገት ብቻ ሳይኾን ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳይ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

52

ባሕር ዳር: ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ ሰብልን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት የግብርና ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድሩ በተሠራው የግብርና ሥራም በምግብ ዋስትና ራስን ለመቻል የሚደረገው ጥረት ውጤት የታየበት ነው ብለዋል።

“ምርት ማምረት ዕድገት ብቻ ሳይኾን ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳይ በመኾኑ ትኩረት የሚጠይቅ ሥራ መከወን ያስፈልጋል” ብለዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ185 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም የለማ ሲኾን ከዚህ ውስጥ ከ91 ሺህ በላይ የሚኾነው በስንዴ ሰብል የተሸፈነ ነው።

በሲያ ደብርና ዋዩ ወረዳ ሮሜ ቀበሌ በ1 ሺህ 300 ሄክታር መሬት ላይ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ ሰብል በርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጎብኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኢንዱስትሪ ዘርፉ ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡
Next article“ዓለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ ኹኔታወችን ለመረዳት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች ወሣኝ ናቸው” የመንግሥት ሠራተኞች