
ባሕር ዳር: ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት የ’World Without Hunger’ ጉባኤን ስናጠናቅቅ፣ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ውይይቶች የተሳኩ ይሆኑ ዘንድ አስተዋፅዖ ያበረከቱትን ተሳታፊዎች ከልብ አመሠግናለሁ ብለዋል።
አርባ ቢሊዮን ዛፎች በተተከሉበት ምርታማነትን በሚያሳድጉ የለውጥ ሥራዎች፣ ድርቅን በሚቋቋሙ አዝርዕት ልማት፣ በአረንጓዴ ዓሻራ መርሃ ግብር ሥራዎች አማካኝነት በዘላቂ የግብርና ሥራ የታየው የኢትዮጵያ ርምጃ በጉባኤው ቀርቧል። በ’ኢትዮዽያ ታምርት’፣ በአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ጥምር የሥራ ፈጠራ ሥራ፣ በገቢ እድገት እና ጽናት የታዩት ኢንቨስትመንቶች በአለም የግብርና ዘርፍ የኢትዮጵያን ሚና አጠናክረውታል።
ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል። ለዚህም ለምግብ ዋስትና የሚሆን የአለምአቀፍ ድጋፍ አቅርቦት፣ ድንበር ዘለል የሆነ የእውቀት ማካፈል ልምምድ፣ ለፍትሃዊ ተደራሽነት የሚረዳ የፖሊሲ መናበብ ብሎም ለሴቶች ትኩረት የሚሰጥ የአነስተኛ አርሶ እና አርብቶአደሮች ድጋፍ ሥራ አስፈላጊ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!