
ደብረ ማርቆስ: ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የህልም ጉልበት ለእመርታዊ ለውጥ በሚል መሪ መልዕክት ለደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና መሪዎች ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ለሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና ቀደም ሲል የተሰጠውን የመሪዎች ሥልጠና ላልወሰዱ መሪዎች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
ሥልጠናው በመሪዎች እና በአባላቱ መካከል ያለውን የአቅም ክፍተት ለመሙላት የሚያግዝ መኾኑን የከተማ አሥተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ስለሽ ተመስገን ተናግረዋል፡፡ ሠልጣኞች ከዚህ በፊት የነበረባቸውን የክህሎት እና የአመለካከት ችግር ቀርፈው የተሻለ አቅም ለመገንባት እና የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንደሚያግዛቸው የከተማ አሥተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ተናግረዋል፡፡
የሥልጠናው ተሳታዎች ሥልጠናው የነበረባቸውን የአቅም እና የአፈጻጸም ጉድለት ለመቅረፍ እንደሚያግዛቸው ነው የገለጹት፡፡ በሥልጠናው ባገኙት ዕውቀትም በተሻለ አቅም ማኅበረሰቡን ለማገልገል ዝግጁ መኾናቸውን አስረድተዋል፡፡
ለደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳዳር ለሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና መሪዎች “የህልም ጉልበት ለእመርታዊ ዕድገት” በሚል መሪ መልዕክት የተሰጠው ሥልጠናም ተጠናቅቋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!