
ደብረ ብርሃን: ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ ሰብልን እየጎበኙ ነው፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ ሰብልን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የአማራ ክልል ዋና አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) እና ሌሎች የክልል እና የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እየጎበኙ ነው፡፡
ጉብኝቱ በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ሮሜ ቀበሌ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!