“ብልፅግና ፓርቲ እጅግ በበዙ ውስብስብና እልህ አስጨራሽ ፈተናዎች የታጀበ የትግል፣ የተግዳሮትና የለውጥ ዓመታትን ያሳለፈ ፓርቲ ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ

88

ባሕር ዳር: ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አመራርና አባላት የብልፅግና ፓርቲ 5ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል አክብረዋል፡፡ “የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚሰጠው የብልፅግና ፓርቲ አባላት 4ተኛ ዙር ሥልጠናም ተጀምሯል።

የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ የተፈጠረው በእልህ አስጨራሽ ትግልና በመስዋዕት ነው ብለዋል። “ፓርቲያችን ብልጽግና ያሳካው ድልም ትልቅ ነው” ሲሉ ገልፀዋል። ብልጽግና ፓርቲ እጅግ በበዙ ውስብስብና እልህ አስጨራሽ ፈተናዎች የታጀበ የትግል፣ የተግዳሮትና የለውጥ ዓመታትን ያሳለፈ ፓርቲ ነው ብለዋል አቶ ይርጋ ሲሳይ፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ከጥንካሬና ድክመቶች በመማር ዘርፈ ብዙ ስኬቶችንም እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ “እንደ ፓርቲ እስካሁን ያልተሻገርናቸው ችግሮች ቢኖርም ከብልፅና አባላት፣ ከደጋፊዎቹና ከመላ ሕዝቡ ጋር በቅንጅት በመሥራት ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን እንዲሆን የማድረግ አቅም ያለው ፓርቲ ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ብልፅግና ኢትዮጵያዊነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ጠብቆ መሥራቱን ይቀጥላል ያሉት አቶ ይርጋ ሲሳይ ለሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬታማነትም ሁሉም ባለድሻ አካል በጋራ እና በትጋት ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል። ከፓርቲው የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በመድረኩ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና ርእዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ስመኘው አጥናፉ፣ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መስፍን አበጀ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ሴቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢሌኒ ዓባይ እንዲሁም ሌሎች አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የጋራ ደኅንነት ላይ አተኩሮ በመሥራት እና ተግባራዊ ጥንቃቄም በማድረግ ባንኩ ተጨባጭ እና ለውጥ ያመጡ ሥራዎችን እየሠራ ነው” አቤ ሳኖ
Next articleበርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም የለማ ሰብልን እየጎበኙ ነው፡፡