ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሠራ መኾኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

55

አዲስ አበባ: ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሠራ መኾኑን የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል። በግብርና ሚኒስቴር የእርሻ እና ሆልቲካልቸር ሚኒስትር ድኤታ መለሰ መኮንን (ዶ.ር) የምግብ እና የሥርዓተ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከክልሎች ግብርና ቢሮ ጋር በመናበብ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

ሚኒስትር ድኤታው በመስኖ ልማት በየዓመቱ ዕድገት እየተመዘገበ ቢኾንም በቂ አለመኾኑን እና ይህንኑ አጠናክሮ ለመሥራት አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መኾኑንም አንስተዋል። የአኩሪ አተር ልማት ትግበራ በኢትዮጵያ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ያሉት ዶክተር መለሰ መስሪያ ቤቱ በዚህም ተስፋ ሰጭ ውጤት ማስመዝገቡን ነው የገለጹት።

ኢትዮጵያ የቅባት እህል በማምረት ከዓለም 23ኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሀገር ናት፤ ምቹ የአየር ንብረት እና አቅም እንደ መኖሩ መጠን እየተሠራ ያለው ሥራ በቂ አለመኾኑንም አብራርተዋል፡፡ ምርት እና ምርታማነትን በማሳደጉ ረገድ ብዙ መሠራት እንዳለበት ሚኒስትር ድኤታው አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች የምታወጣውን ከፍተኛ ወጭ ለመቀነስ በሀገር ውስጥ ምርት መተካት በሚል ከተጠሪ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ጋር የግብርና ምኒስቴር ምክክር አድርጓል።

ዘጋቢ፡- አየለ መስፍን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለውጥ ማስመዝገብ ከተፈለገ ቁርጠኛ ልብ እና ሥራን ሳይንቁ መሥራት ያስፈልጋል” በዶሮ እርባታ የተሰማሩ እናት
Next article“የጋራ ደኅንነት ላይ አተኩሮ በመሥራት እና ተግባራዊ ጥንቃቄም በማድረግ ባንኩ ተጨባጭ እና ለውጥ ያመጡ ሥራዎችን እየሠራ ነው” አቤ ሳኖ