የጊኒው ጠቅላይ ሚኒስትር አማዲ ኡሪ ባህ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚን ጎበኙ።

41

ባሕር ዳር: ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የጊኒው ጠቅላይ ሚኒስትር አማዲ ኡሪ ባህ የ2024 የዓለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ዋንጫ አህጉራዊ ሻምፒዮና ማጠቃለያ ፕሮግራም ለመታደም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በቦታው ሲደርሱ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በማጠቃለያው ፕሮግራሙ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የስፖርት ማኅበራት ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተገኘውን አንፃራዊ ሰላም በዘላቂነት በማጽናት በሙሉ አቅም ወደ ልማት መግባት እንደሚያስፈልግ እንድሪስ አብዱ አሳሰቡ።
Next articleለመልሶ ልማት ሥራዎች እና ለሰው ተኮር ፕሮጄክቶች ትኩረት መሰጠቱን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ::