
ባሕር ዳር: ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የኮሎምቢያ ዋና ከተማ ቦጎታ የቀድሞ ከንቲባ እና ለከተሞች ዕድገት እና ስማርት ሲቲ መረጋገጥ የገንዘብ እና መሰል ድጋፍ በማድረግ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው የቢግዊንስ ፕሮጀክት አስተባባሪ ኤንሪክ ፔናሎሳ የባሕርዳር የኮሪደር ልማት ሥራን ጎብኝተዋል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና የሥራ ባልደረቦቻቸው እየተሠሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን አስጎብኝተዋል፡፡
የኮሎምቢያ ዋና ከተማ ቦጎታ አሁን ለደረሰችበት ሁለንተናዊ ልማት እና ዕድገት ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የቀድሞ ከንቲባዋ እና የአሁኑ የቢግዊንስ ፕሮጀክት አስተባባሪ ኤንሪክ ፔናሎሳ ያላቸውን የካበተ ልምድ ለማካፈል መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
ኤንሪክ ፔናሎሳ ያላቸውን ልምድ ከያዙት ቢግዊንስ ፕሮጀክት ጋር በማስተሳሰር ለባሕርዳር ከተማ ልማት እና ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ከጉብኝት በኋላ ከተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ጋር ባደረጉት ውይይት መግለጻቸውን ከባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!