ዶናልድ ትራምፕ ዳግም ወደ ኃይትሀውስ የመመለሳቸውን ነገር አረጋግጫለሁ እያሉ ነው።

54

ባሕር ዳር: ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ዙር የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ኾነው መግባታቸው ጉዳይ እንዳረጋገጡ ለደጋፊዎቻቸው በመግለጽ የደስታ መግለጫቸውንም እያቀረቡ ነው።

ሪፐብሊካኑ ትራምፕ ከዲሞክራቷ ሀሪስ ጋር የምርጫ ትንቅንቅ እያደረጉ ቢኾንም መሪነቱ በትራምፕ እጅ እንደኾነ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሚዲያዎች ሁሉ እየዘገቡት ነው።

የትራንፕ ማሸነፍ ዕውን ከኾነ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ኾነው ወደ መንበረ ሥልጣኑ ዳግም ይመለሳሉ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ ሕዝባዊ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ.ር) ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።