
ደብረ ብርሃን: ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ በሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ ሾላ ገበያ ከተማ ነው እየተካሄደ ያለው። በውይይቱ ከወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።
ውይይቱን በሀገር መከላከያ ሠራዊት የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ እና የሰሜን ሸዋ ዞን አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ እየመሩት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!