የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አጓጊ ኾኖ ቀጥሏል።

22

ባሕር ዳር: ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የዓለምን ትኩረት የሳበው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቱ አጓጊ ኾኖ እንደቀጠለ ነው።

ውጤቱ በፍጥነት ተለዋዋጭ ቢኾንም በምርጫው እስካሁን ድረስ ዶናልድ ትራምፕ በ230 ለ210 በኾነ ውጤት ካማላ ሀሪስን እየመሩ ነው።

ትራምፕ በ23 ግዛቶች ድል ሲቀናቸው ሀሪስ ደግሞ በ13 ግዛቶች አሸንፈዋል። በዚህ ተጠባቂ ምርጫ 270 የወኪል መራጮችን ድምፅ ያገኘ እጩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ይኾናሉ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሕዝብን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት እየተሠራ ነው ” አቶ እንድሪስ አብዱ
Next articleበአማራ ክልል ከ488 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በቡና ልማት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ግብርና ቢሮ ገለጸ።